ኡቡንቱ አፍሪካዊ ባህል ነው። በአንድ ወቅት አንድ አንትሮፖሎጂስት ለጥናት በመጣበት አፍሪካ አንድ መንደር ውስጥ ተሰብስበው ሲጫውቱ ለነበሩ የአንድ ጎሳ ታዳጊዎች ለጨዋታ የሚሆን ሃሳብ ያቀርባል። በጣፋጭ የተሞላ ቅርጫት 100 ሜትር ራቅ ያለ ዛፍ ስር አስቀመጠና ለልጆቹ በሩጫ ውድድር 1ኛ የሚወጣው ልጅ መውስድ አንደሚችል ይንግራቸዋል። ከዚያም 1…2…3 ብሎ ቆጥሮ ውድድሩን ያስጀምራል።

ልጆቹ ምን አደረጉ?

ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው በአንድት መሮጥ ይጀምራሉ። ዛፉ ስር የተቀመጠው ጣፋጭ ጋር እኩል ደርሰው እኩል ተካፍለው እያጣጣሙ መብላት እና በጣእሙ መደሰት ይጀምራሉ። ይህን ያየው አንትሮፖሎጂስት በልጆቹ ሁኔታ ተገርም ለምን እንዲህ እንዳደርጉ ሲጠይቃቸው፤

‘’ኡቡንቱ” ብለው በአንድ ድምጽ ይመልሱለታል።

ምን ማለታቸው ነው? – “ሁሉ ሰው አዝኖ እንዴት አንድ ሰው ብቻውን ደስተኛ ሊሆን ይችላል?”

ኡቡንቱ ማለት በእነርሱ ቋንቋ – “የእኔ ስሜት የሚቀዳው ከእኛ ስሜት ውስጥ ነው” (I am because we are) እንደማለት ነው።