Asset Based Community Development (ABCD) በሚል ስያሜ የሚታወቀውን የማህበረሰብ ልማት ውጤታማ ዘዴ የነደፉት ጆን ማክኒት እና ጆዲ ክሬትስማን ሲሆኑ ዘዴው በግለሰቦች እና በማህበረሰቦች ውስጥ አስቀድሞ ባለው ሀብት ላይ መሰረት በማድረግ በጋራ ልማትን ማረጋገጥ ላይ ያተኩራል። በዚህ ዘዴ ሀብት ተብለው የሚጠቀሱት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ችሎታዎች፣ ተሰጥኦዎች፣ ስጦታዎች፣ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ባህል፣ ልማድ እና ወግ፣ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች ወይም ማህበራት ሊያበረክቱት የሚችሉት ማንኛውም በጎ አስተዋፅዖች ናቸው። ሂደቱ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች (ነዋሪዎች) የሚመራ ሲሆን ነዋሪዎች ግለሰቦች ችሎታቸውን፣ ልምዳቸውን፣ እውቀታቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ እና የማይተካ የለውጥ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል እድል ይሰጣል።